መጋ 3 ቀን 2000 ዓ.ም


ማርታ እንድርያስ

በሚሌኒየሙ የሴቶችን አቅም ለማጎልበት የሚደረገውን ጥረት ለማጎልበት በማህበር ተደራጅተው መብትና ጥቅሞቻቸውን የሚያስከብሩበት ሁኔታ መመቻቸት እንደሚገባው የአዲስ አበባ ሴቶች ማህበር ምክትል ሊቀመንበር አመለከቱ፡፡

ምክትል ሊቀመንበር ወ/ሮ ማንያህልሻል ግርማ በቅርቡ በተለያዩ ዝግጅቶች የተከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት እንደተናገሩት በሚሌኒየሙ የሴቶችን አቅም ለማጎልበት የሚደረገው ጥረት እንዲሳካ በማህበር በመደራጀት መብትና ጥቅሞቻቸውን ሊያስከብሩ ይገባል፡፡

ማህበሩ በዚህ በኩል እያከናወናቸው ስላሉ ተግባራት ሲያብራሩም የሴቶችን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም ሊያጎለብቱ የሚችሉ የተለያዩ ኘሮግራሞችን ለመንደፍና የአገልግሎቱን በስርአት ለማዳረስ በማህበር የሚደራጁበትን ሁኔታ እያመቻቸነው ብለዋል፡፡

የሴቶች በማህበር መደራጀት ለሚገጥሟቸው ችግሮች በጋራ መፍትሔ ለማፈላለግ ይረዳል የሚሉት ምክትል ሊቀመንበር በየትኛውም ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶች ወደ ማህበሩ በመምጣት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

 

 

 

 

<< Back to Home >>

 
 
 
 
Addis Millennium Bottum