የካቲት 20 ቀን 2000 ዓ.ም
ቁምላቸው አበበ
የሚሌኒየሙ 12ኛ አዲስ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ትላንት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ፡፡
ላለፉት ሰባት ቀናት በኤግዚብሽን ማዕከል ለህዝብ ክፍት ሆኖ የቆየውን የንግድ ትርዒት ከ100 ሺህ በላይ ሕዝብ እንደጐበኘው ተመልክቷል፡፡
በንግድ ትርዒቱ 300 አገልግሎት ሰጭ፣ አምራቾችና የንግድ ተቋማት የተሳተፈ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የውጭ ሀገራት ድርጊቶች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤትን ጨምሮ ከ25 በላይ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎታቸውንና ተግባራቸው ያስተዋወቁበትን ፖቫሊዮን ከ25 ሺህ በላይ ሕዝብ በላይ ሕዝብ እንደጐበኘው ተመልክቷል፡፡
አዲስ ቻምበር ባዘጋጀው የሚሌኒየሙ አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት የአዲስ አበባ ፖቪሊዮን የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት ባሳየው ከፍተኛ እንቅስቃሴ መሆኑ ይታወሳል፡፡
<< Back
to Home >> |