መጋ 06 ቀን 2000 ዓ.ም


ያረጋል የኋሌ

በሚሌኒየሙ ድህነትን ለመቀነስ በሚደረገው እንቅስቃሴ ትምህርት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተገለፀ፡፡

የሽመልስ ሀብቴ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚሌኒየም በዓልን ትናንት በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ባከበረበት ወቅት የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ስዩም አእምሮ እንደገለፁት ድህነትን በማስወገድ ዕውቀት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

ለዚህም ትምህርት ቤቶች በስነ ምግባር የታነፀ ትውልድ በማፍራት የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው መቀጠል ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡

በተለይ በአገር አቀፍ ደረጃ የታለመውን ውጤት ለማግኘት ተማሪዎች፣ ወላጆችና መምህራን ይበልጥ ተቀራርበው በመስራት ለመማር ማስተማሩ ስኬታማነት በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በበአሉ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኪሮስ ኃ/ስላሴ በበኩላቸው በየትምህርት ቤቱ እየተከበረ ያለው የሚሌኒየም በአል የተለየ መነቃቃትን ፈጥሯል፡፡

ስለሆነም የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅና የነገ አገር ተረካቢ ትውልድን ለማፍራት ይህን መልካም አጋጣሚ ባለድርሻ አካላትና በአጠቃላይ ህብረተሰቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

 

 

 

 

<< Back to Home >>

 
 
 
 
Addis Millennium Bottum