መጋቢት 1 ቀን 2000 ዓ.ም
ቁምላቸው አበበ
በሚሌኒየሙ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፖኬጆችን ተግባራዊነት ለማረጋገጠ የወላጆች ተሳትፎ የማይተካ አስተዋፅኦ እንዳለው የተለያዩ ት/ቤቶች ርዕሳነ መምህራን አስታወቀ፡፡
የከፍተኛ 20 መካከለኛ ደረጃ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም ርዕሰ መምህር አቶ አለሙ አፅበሀ ሰሞኑን እንዳሰታወቁት የትምህርት ጥራቱን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ከዕቅድ እስከ አፈፃፀም የሚሳተፉበት ስልት ሊቀየስ ይገባል፡፡
የሕዝበ አምባ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር ወ/ሮ ጥሩነሽ ደሱ በበኩላቸው ወላጆች የልጆቻቸውን የዕለት ተዕለት የትምህርት ውሎ በመከታተልና ከትምህርት ቤቱ የቀረበ ግንኙነት በመፍጠር ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ አስተዋፆ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የግንቦት 20 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ አለሃ አብርሃ እንደገለፁት ወላጆች የትምርት ጥራት ማሻሻያ ፖኬጆች ላይ የጠራ ግንዛቤ እንደኖራቸውና በአፈፃፀሙ እንዲሳተፍ ትምህርት ቤቱ ጥረት በማድረግ ላይ ነው፡፡
የክሩዝ አካዳሚ ወላጆች ኮሚቴ ሰብሳቢ ሻምበል ስዩም ዘለቀ በበኩላቸው ወላጆች ልጆቻቸው የሚማሩበትን ትምህርት ቤት የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መከታተልና በትምህርት ጥራቱ የበኩላቸውን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ወላጆች ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ጋር የቀረበ ግንኙነት ማድረግና መከታተል በመቻላቸው የትምህርት ጥራቱን ማሻሻል መቻላቸውን ሰብሳቢው ተናግረዋል፡፡
<< Back
to Home >> |