የካቲት 25 ቀን 2000 ዓ.ም
ያረጋል የኋሌ
አገራችን በአበረታች የንግድና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ ከተለያዩ የውጭ አገራት የመጡ ባለሀብቶች ገለፁ፡፡
12ኛውን የሚሌኒየሙን አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ለመሳተፍ ከሱዳን፣ ግብፅ፣ ጅቡቲ፣ ሳውዲ አረብያና ህንድ የመጡ ተሳታፊ ባለሀብቶች እንዳስታወቁት አገራችን በአጭር ጊዜ ውስጥ የአስመዘገበቻቸው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች አበረታች ናቸው፡፡
በተለይም በንግድና ኢንቨስትመንት የስራ ዘርፍ እየታየ ያሉ ለውጦች የውጭ ባለሀብቶችን የሚስብና ለበለጠ ስራ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል፡፡
ይህ ሁኔታም አገራቱ በአበባ፣ ቡና፣ በቆዳና ሌጦ፣ በጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዲሁም በቅባት እህሎች በአለም ገበያ ብቁ ተወዳዳሪነቷን በአጭር አመታት እንደምታረጋግጥ አመላካች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
12ኛ የሚሌኒየሙ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢት ዝግጅት በተሳታፊ ብዛት፣ እራስን በማስተዋወቅና በጋራ ለመስራት ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረላቸውም ጠቁመዋል፡፡
በአለም ዓቀፍ ንግድ ትርኢቱ 300 ያህል ተሳታፊዎች የነበሩ ሲሆን 150 ያህሉ ከ23 የተለያዩ አገራት የመጡ መሆናቸውንና ይህ አሀዝም ከዚህ በፊት ከነበሩት ደንበኞች መጨመሩንም ከንግድ ትርኢቱ የስራ ኃላፊዎች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
<< Back
to Home >> |