ሚያዚያ 8 ቀን 2000 ዓ.ም

ቁምላቸው አበበ

በሚሌኒየሙ በአዲስ አበባ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት የሰንደቅ ዓላማና የብሔራዊ ሕዝብ መዝሙር አከባበር ስነ-ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተመለከተ፡፡

በአዲስ አበባ ጊዜአዊ ባለአደራ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀጐስ ሀይሉ ሰሞኑን እንዳስታወቁት የነገ ሀገር ተረካቢ ሕፃናትና ወጣቶች ስለሀገራቸው ባንዲራ ያላቸውን ግንዛቤ ለማጐልበት የተቀናጀ የማስተማርና የማስተዋወቅ ስራ በመጀመር እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው፡፡

የማንነታችን መገለጫ የሆነውን የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ትርጉም ሕጻናትና ወጣቶች በውል እንዲረዱት በየደረጃው የሚገኙ የግልና የመንግስት የትምህርት ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ማካሄድ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በየትምህርት ተቋማቱ የሰንደቅ ዓላማና የብሔራዊ መዝሙር ስነ-ስርዓት ሊካሄድ እንደሚገባም ተመልክቷል፡፡

በአንዳንድ ት/ቤቶች የሰንደቅ ዓላማና የብሔራዊ መዝሙር ስነ-ስርዓት ተግባራዊ በመደረግ ላይ እንደሚገኝም አቶ ሀጐስ ጠቁመዋል፡፡

ሌሎች የትምህርት ተቋማትም ይህን አርአያ በመከተል ሥነ-ሥርዓቱን ተግባራዊ ማድረግ እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በመጭው ግንቦት ወር የሚሌኒየም የሰንደቅ አላማ ቀን ለማክበር በአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት አማካኝነት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች የተሳተፉበት ውይይት ሰሞኑን መካሄዱ ይታወሳል፡፡

 

 

 

 

<< Back to Home >>

 
 
 
 
Addis Millennium Bottum