ሰኔ 12 ቀን 2000 ዓ.ም


ቁምላቸው አበበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ም/ቤት ጽ/ቤት የታዳጊ ክልሎችን ገጽታ ለመገንባት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡

የብሔራዊ፣ የአዲስ አበባና የክልል ሚሌኒየም ጽ/ቤት ትላንት በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ም/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ስዩም በረደድ እንዳስታወቁት በሚቀጥሉት ወራት የጋምቤላን፣ የቤኒሻንጉል ጉምዝን፣ የሶማልያንና የአፋር ክልሎች ዕምቅ የቱሪስት መስህቦችና የኢንቨስትመንት አማራàች የማስተዋወቅ ስራ ይከናወናል፡፡

ታዳጊ ክልሎች ተፈጥሮአዊ፣ ባህላዊና ሰው ሰራሽ መስህቦችና በስፋት ለማስተዋወቅ የሚያግዙ የገጽታ ግንባት ስራዎች ይከናወናሉ ብለዋል፡፡

በሚሌኒየሙ የእነዚህን ክልሎች ዕምቅ የኢንቨስትመንት ሀብት በማስተዋወቅ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሀብቶችን ለመሳብ ጥረት እንደሚደረግም አቶ ስዩም ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባና ብሔራዊ ሚሌኒም ከአያት አክሲዎን ማህበር ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማና ብሔራዊ መዝሙር ቀን በዓልን ለማክበር የሚያደርጉት ዝግጅት በተያዘለት መርህ ግብር መሰረት በመከናወን ላይ እንደሚገኝ አስታውሰዋል፡፡

ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆን የፌደራል ሰንደቅ ዓላማ ህትመት በመፋጠን ላይ ሲሆን የብሔራዊ መዝሙር ሲዲ እንዲሁም ስለ ሰንደቅ ዓላማ ቀን ምንነት የሚገልጽ ጽሑፍ ዝግጅት በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የሀገር ውስጥም ሆኑ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ከዋዜማው ጀምሮ ስለሚሌኒየሙ በዓል አከባበር ሰፊ ሽፋን መስጠታቸው የሀገሪቱን ገጽታ በመቀየር ረገድ የላቀ አስተዋፆ ማበርከቱን አቶ ስዩም አውስተው መገናኛ ብዙሃን በቀጣይም ከዜና ባለፈ ትኩረት በመስጠት ተከታታይነት ያለው የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጡ አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ም/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ነጸነት አስፋው በበኩላቸው ዜጐች ስለ ሀገራቸው ሰንደቅ አላማ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና ሰንደቅ ዓላማውን እንዲያከብሩ በትምህርት ቤቶች ሰፊ የማስተማርና የመቀስቀስ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

 

 

 

<< Back to Home >>

 
 
 
 
Addis Millennium Bottum