የካቲት 27 ቀን 2000 ዓ.ም
ቁምላቸው አበበ
የሚሌኒየሙ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን የሴቶችን መብቶችና ጥቅሞች ለማስከበር የወጡ ሕጐችን ማስገንዘብ በሚያስችሉ የተለያዩ ዝግጅቶች ከነገ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በመዲናችን እንደሚከበር ተገለፀ፡፡
በአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት የትዕይንቶች ኤክስፐርት አቶ ዘካርያስ ካሱ ዛሬ እንዳስታወቁት የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሴቶች ቀን በእግር ጉዞ፣ በውይይትና በሴቶች ምክክር ያከብራል፡፡
የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት ከ #ጄንደር ቤዝድ ቫዮለንስ ካምፔይን$ ጋር በመተባበር ነገ መነሻውን አራት ኪሎ መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የእግር ጉዞ ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ እንደሚያካሂድ ኤክስፐርቱ ጠቁመዋል፡፡
#ሴቶችን እናክብር እናወድስ$ በሚል መርህ በሚካሄደው የእግር ጉዞ ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ዘካሪያስ አስታውቀዋል፡፡
የፊታችን ቅዳሜ ጽ/ቤቱ ከአዲስ አበባ ነጋዴ ሴቶች ማህበር ጋር በመተባበር ሴቶችን በሚመለቱ ፖሊሲዎች ላይ በአዲስ አበባ አስተዳደር ም/ቤት አዳራሽ ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡
እሁድ የካቲት 30 በኢትዮጵያ ስብሰባ ማዕከል ከ1 ሺህ በላይ ሴቶች በሚሳተፉበት ገርልስ ፎረም ላይ በሚቀርቡ ጥናታዊ ፅሑፎች ውይይት እንደሚካሄድና ዝግጅቱ ቀጥታ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ሽፋን እንደሚያገኝም አቶ ዘካርያስ አስታውቀዋ፡፡
<< Back
to Home >> |