መጋቢት 19 ቀን 2000 ዓ.ም
ያረጋል የኋሌ
በአዲሱ ሚሌኒየም በተለያየ ወቅት የሚዘጋጁ የንግድ ትርኢቶች፣ ባዛሮችና ኤግዚቢሽኖች ሸማቹን ህብረተሰብና ነጋዴውን በማገናኘት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸው ተገለፀ፡፡
በአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰለሞን መንግስተ አብ እንደገለፁት፣ በያዝነው የሚሌኒየሙ አመት በርካታ የንግድ ትርኢቶች ተዘጋጅተዋል፡፡
እነዚህ የንግድ ትርኢቶች አምራቾችን፣ አከፋፋዬችንና አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን እርስ በእርሳቸው ከማስተዋወቁም በተጨማሪ ከሸማቹ ህብረተሰብ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ለመፍጠር ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡
ይህም እያንዳንዱ የምግብ አይነቶች፣ የሸቀጣ ሸቀጥ፣ አልባሳት፣ የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶችና ሌሎች የፋብሪካ ምርቶች አይነትና የጥራት ደረጃ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ባለሙያዎችና ተጠቃሚዎች በሚገባ ለመለየት እንደሚያስችላቸው ገለፀዋል፡፡
የንግድ ትርኢቶች፣ ባዛሮችና ኤግዚቢሽኖች በተለያየ ደረጃ መዘጋጀታቸው የአገርን መልካም ገፅታ በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ የገለፁት አቶ ሰለሞን በቅርቡ 12ኛው የሚሌኒየሙ አዲስ ቻምበር አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት በኤግዚቢሽን ማዕከል ሲዘጋጅ የተስተዋለ ይሄው እውነታ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡
<< Back
to Home >> |