መጋቢት 17 ቀን 2000 ዓ.ም
ያረጋል የኋሌ
በአዲሱ ሚሌኒየም የመርካቶን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚያስቃኝ የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን ተከፈተ፡፡
በአሜሪካ ኤምባሲ የባህል ተቋም የተዘጋጀው ይህ ኤግዚቢሽን ከ50 የላነሱ የመርካቶን የስራ ሂደት የሚያሳዩ ፎቶ ግራፎች ተካተውበታል፡፡
ኤግዚቢሽኑ ከመጋቢት 16 እስከ 24 2000 ዓ.ም ለጐብኝዎች ክፍት የሚሆን ሲሆን በትናንትናውና በዛሬው ዕለት በቀን ከ100 ያላነሱ ተመልካቾች እንደሚመለከቱት ታውቋል፡፡
አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች እንደገለፁት የዚህ አይነት የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን በሚሌኒየሙ ለመጀመሪያ ጊዜ በመርካቶ መዘጋጀቱ ለንግድ እንቅስቃሴው ውጤታማነት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል፡፡
የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽኑ ሊዘጋጅ የቻለው አንድ አሜሪካዊ ፎቶ ግራፈር የመርካቶን የንግድ ስራና አሰራርን ተመልክቶ በካሜራ ያነሳውን ፎቶ ግራፍ አሰባስቦ ለእይታ በማብቃቱ እንደሆነ ከአሜሪካ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡
ኤግዚቢሽኑን በይፋ መርቀው ለተመልካች ክፍት ያደረጉት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ሚስስ ዲቦራህ አር-ማላክ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
<< Back
to Home >> |