መጋቢት 18 ቀን 2000 ዓ.ም
ያረጋል የኋሌ
በአዲሱ ሚሌኒየም የአገልጋይነት ስሜትን ያዳበረ ሲቪል ሰርቪስ አመራር የመገንባት እንቅስቃሴው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቆመ፡፡
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ በጊዮን ሆቴል ባዘጋጀው የሁለት ቀን አውደ ጥናት ላይ ያነጋገርናቸው የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ማስረሻ እንደገለፁት የሲቪል ሰርቪስ ዘመናዊ አሰራር ውጤታማ እንዲሆን ከአገልግሎት ሰጭው ሰራተኛ ብዙ ይጠበቃል፡፡
በእስካሁ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ኘሮግራመ ላይ አበረታች ውጤት የተገኘ ሲሆን በአዲሱ ሚሌኒየም አሰራሩን ይበልጥ አጠናክሮ ለመቀጠል የመንግስት አካላትና ህብረተሰቡ ይበልጥ ተቀራርበው መሰራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
ዛሬ በተጀመረው የሁለት ቀን አውደ ጥናት በስነ ምግባር፣ የሰራተኞች ፍልሰት፣ የሲቪል ሰርቪስ አተገባበርና በሌሎችም ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በባለሙያዎች አምስት ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚቀርብ ጠቁመዋል፡፡
ከዚህም የሚገኘው ውጤት ለመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጀ ቀረፃ አጋዥ ሆኖ የሚቀርብበት ሁኔታ ከወዲሁ እንደሚመቻችም አቶ ሰለሞን ገልፀዋል፡፡
በዚህ አገር አቀፍ አውደ ጥናት ላይ ከ80 በላይ የፊዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲዎች፣ የክልል ቢሮዎችና ኮሚሽኖች የተውጣጡ ባለሙያዎች ማሳተፋቸውን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
<< Back
to Home >> |