27 ቀን 2000 ዓ.ም


ማርታ እንድርያስ

ሚሌኒየሙን በማስመልከት የብሔር ብሔረሰቦችን አኗናር በሚያንፀባርቅ መልኩ አዲስ አበባ ላይ የሚገነባው የሚሌኒየም መንደር ከቱሪስ መስህብነት ባሻገር ለከተማይቱ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጭ እንደሚፈጥር ተገለፀ፡፡

ኢትዮጵያን ቪሌጅ የተሰኘው ድርጅት ከአዲስ አበባ ሚሌኒየም ፅ/ቤት፣ ከክልል መንግስታት እና ከተለያዩ የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር ቦሌ አካባቢ የሚያስገነባው የሚሌኒየም መንደርን በተመለከተ ዛሬ በሸራተን ሆቴል በጠራው ስብሰባ ላይ የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሙራድ መሀመድ እንደተናገሩት ሚሌኒየሙን ምክንያት በማድረግ የሚገነባው ይህ መንደር ለኢንቨስትመንትና ለቱሪስት መስህብ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡

በስፍራው ብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ማንነታቸውን የሚያፀባርቁ ልዩ ልዩ ባህላዊ ቁሳቁሶችነና ምግቦችን ለሽያጭ እንደሚያቀርቡና ይህም የኢንቨስትመንት አማራጭ ከማስገኘቱ ባሻገር በስፍራው የሚያፀባርቀው የብሔር ብሔረሰቦች ባህል ኢትዮጵያን ተዘዋውረው ለማየት በቱሪስቶች ዘንድ ጉጉት እንደሚፈጥር አቶ ሙራድ አስረድተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኪሮስ ኃ/ስላሴ በበኩላቸው በሚሌኒየሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለውን የገፅታ ግንባታ የሚጠናክረውን ይህን ተግባር የዜጎችን ትብብር የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም ወገኖች የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 02 አድዋ ፖርክ እየተባለ በሚጠሪው 160 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈውን መንደር በመጪው ግንቦት 20 ለማስጀመር እቅድ እንዳለም በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡

 

 

 

<< Back to Home >>

 
 
 
 
Addis Millennium Bottum