መጋ 3 ቀን 2000 ዓ.ም


ያረጋል የኋሌ

በንግድና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በሚሌኒየሙ በአለም ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን በአገር ውስጥና በውጭ አገር በሚካሄዱ የንግድ ትርኢቶች የመሳተፍ ባህላቸውን ሊያጐለብቱ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የአዲስ አበባ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ምክትል ዋና ፀሐፊና የአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታምራት አድማሱ እንደገለፁት የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ምርትና አገልግሎታቸውን በስፋት የማስተዋወቅ ሥራ ሊያከናወኑ ይገባል፡፡

አገራችን በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ሊያደርጓት የሚችሉ በርካታ የንግድና የኢንቨስትመንት አማራàች ያሏት በመሆኑ በእነዚህ የሥራ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሀብቶች በተለያዩ አካባቢዎች እየተዘዋወሩ ምርታቸውን በማቅረብ ተቀባይነትን ማጐልበት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

በተለይም በአዲሱ ሚሌኒየም በሁሉም አቅጣጫ የተፈጠረውን መነቃቃት በመጠቀም ከዘርፍ የሚገኘውን ጠቀሜታ ለማሳደግ ከግል ባለሀብቶች ብዙ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

በአገራችን የሚገኙ በንግድና ኢንቨስትመንት ሥራ የተሰማሩ ባለሀብቶች በአገር ውስጥና በውጭ በሚከናወኑ ታላላቅ የንግድ ትርኢቶች የመሳተፍ ባህላቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጐለበተ እንደመጣ የተናገሩት አቶ ታምራት ይህ እንቅስቃሴ በአዲሱ ሚሌኒየም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በቅርቡ በአገራች የተካሄደው 12ኛው የሚሌኒየሙ አለም አቀፍ የንግድ ትርኢት 50 በመቶ ያህሉ የአገር ውስጥ ተሳታፊ ሲሆኑ ይህም ከአመት አመት በንግድ ትርኢት የመሳተፍ ፍላጐታቸው እያደገ መምጣቱን ለውጡ የሚያስደስት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

 

 

<< Back to Home >>

 
 
 
 
Addis Millennium Bottum