መጋ 26 ቀን 2000 ዓ.ም

ያረጋል የኋሌ

አዲሱ ሚሌኒየም በአል አከባበር ለህፃናት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት የአዘጋጀው የህፃናትና የቤተሰብ ፌስቲቫል በሀይማኖት መሪዎች አድናቆት አገኘ፡፡

የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት መጋቢት 24/2000 ዓ.ም ለሀይማኖት መሪዎችና ለመንግስት ባለስልጣናት የአዘጋጀው የአገር በቀል የህፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ጉብኝት ኘሮግራም ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ äውሎስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ኘሬዚዳንት ሼህ ኤልያስ ሬድማንና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊ ቤተ-ክርስቲያን ጳጳስ አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል እንደገለፁት ጽ/ቤቱ የሚያከናወናቸው ተግባራት የሚደነቁ ናቸው፡፡

በተለይም በአዲሱ ሚሌኒየም ለህፃናት ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ የዚህ አይነት የጉብኝት ኘሮግራም ማዘጋጀቱ የሀይማኖት ተቋማት እገዛ እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል፡፡

የሀይማኖት ተቋማት መሪዎች በተዘጋጀው የጉብኝት ኘሮግራም መደሰታቸውን ገልፀው፣ እንደዚህ አይነት ተቋማትን ይበልጥ ለማጠናከር አቅም የፈቀደውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

የአዲሰ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት በዚህ መልክ የሚያደርገውን የማስተባበር፣ በህፃናት ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ተቋማትን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የማገናኘቱ ተግባር ይበልጥ አጠናክሮ ሊቀጥልበት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

 

 

 

 

<< Back to Home >>

 
 
 
 
Addis Millennium Bottum