ሚያዚያ 22 ቀን 2000 ዓ.ም
ያረጋል የኋሌ
በአዲሱ ሚሌኒየም ኤች. አይ. ቪ ኤድስን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን ህብረተሰቡ የደም ምርመራ ማድረግን እንደባህል አድርጐ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ ተመለከተ፡፡
በዘውዲቱ ሆስፒታል የኤች. አይ.ቪ/ኤድስ የደም ምርመራና የህክምና ማዕከል ኃላፊ ዶ/ር አስቴር ሸዊ አማረ እንደገለፁት የኤች. አይ. ቪ የደም ምርመራ ማድረግ ኤድስን የመከላከሉ እንቅስቃሴ ውጤታማ እንዲሆን ያስችላል፡፡
በእስካአሁኑ ሂደት ህብረተሰቡ የኤች. አይ. ቪ/ኤድስ የደም ምርመራ አድርጐ ራሱን የማወቅ ፍላጐቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የገለፁት ዶ/ር አስቴር ይህ ሁኔታም በአዲሱ ሚሌኒየም ቀጣይ አመታትም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
በዘውዲቱ ሆስፒታል የደም ምርመራና የህክምና ማዕከል የተጠቃሚ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንና በዚህ ረገደም አበረታችና የባህሪ ለውጥ ጅምሮ እንቅስቃሴ መገኘቱን እንደሚያመላክት ገልፀዋል፡፡
ይህ ውጤት ቀጣይነት እንዲኖረው የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች አሁን እያደረጉት ያለውን የማስተማር፣ የማሳወቅና የማንቃት ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመስኩ የተሰማሩ ባለሙያዎችም ትኩረታቸውን በኤች. አይ. ቪ/ ኤድስ ላይ አድርገው የሚሰሩ ጋዜጠኞችን በመቅረብ፣ በማማከርና ኤች. አይ. ቪ/ኤድስን አስመልክቶ በሚነሱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሙያዊ ማብራሪያና ትንታኔ በመስጠት ሊተባበሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
<< Back
to Home >> |