ሰኔ 9/2000 ዓ.ም
ያረጋል የኋሌ

“ሶስት ዛፍ ለሶስት ሺ” ፕሮጀክት የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ሰራተኞችና የአገርህን እወቅ ክበብ አባላት የችግኝ ተከላ ስነ ስርዓት አከናወኑ፡፡

ትናንት በሚሌኒየም ፓርክ በተከናወነው የችግኝ ተከላ ከ 250 በላይ የኮሚሽኑ ሰራተኞችና የአገርህን እወቅ ክበብ አባላት ተገኝተው አገር በቀል የዛፍ ችግኝ ተከላ አከናውነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴወድሮስ ዘውዴ በእለቱ እንደገለፁት የሚሌኒየሙን በዓል አከባበር ተከትሎ በሕብረተሰቡ ተሳትፎ እየተተከሉ ያሉ ችግኞች የአካባቢያችንን ስነ ምህዳር ለመጠበቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የሀይል አቅርቦትን በማስተካከል ዛፎች ትልቅ ጠቀሜታ እንዳላቸው የተናገሩት አቶ ቴወድሮስ ሦስት ዛፍ ለሦስት ሽ ፕሮጀክት ውጤታማ እንዲሆን እያንዳንዱ ግለሰብ ተሳትፎውን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

በችግኝ ተከላው ወቅት ስለ አተካከሉ በእለቱ ለተገኙ የችግኝ ተከላው ተሳታፊዎች በባለሙያ ገለፃ ተደርጎላቸው የችግኝ ተካላ ስነስርአቱ እንደተከናወነ በስፍራው ተገኝተን ለመመልከት ችለናል፡፡

 

 

<< Back to Home >>

 
 
 
 
Addis Millennium Bottum